መግቢያ

የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂና የከተማ ልማት ፖሊሲ ላይ ተመስርቶ የራሱ ፕሮግራምና ዝርዝር የድጋፍ ፓኬጅ ተዘጋጅቶለት ላለፉት አመታት በኢንተርፕራይዞች ልማት አበረታች ውጤት አስገኝቷል፡፡ የድጋፍ ፓኬጁም በተመረጡ ዕድገት ተኮር ዘርፎች ላይ በማተኮር ለኢንተርፕራይዞች ድጋፍ መስጠት አስችሏል፡፡ በዚህም መሠረት በተለያዩ የምርትና የአገልግሎት ሙያዎች ለተሠማሩ በርካታ ኢንተርፕራይዞች አስፈላጊው የማደራጀት፤ የማሰልጠን፣ የፋይናንስና እንዲሁም የማምረቻና የመሸጫ ቦታ አቅርቦቶች እና የገበያ ትስስር ድጋፎች እንዲያገኙ በማድረግ ሰፊ የስራ ዕድል እንዲፈጠርና ለድህነት ቅነሳ ፕሮግራሙ የራሱን አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡

ሆኖም የተሰጡት ድጋፎች ኢንተርፕራይዞቹ በየዕድገት ደረጃቸው ለሚያጋጥሟቸው ችግሮች መፍትሄ በመስጠት ረገድ ውሱንነት ታይቶባቸዋል፡፡ በዚሁ መሰረት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ስትራቴጂ የድጋፍ ማዕቀፍና የአፈፃፀም ስልቶች ሰነድን መሠረት በማድረግ ኢንተርፕራይዞችን እንደየዕድገት ደረጃቸው በመክፈል የተቀመጡ ሲሆን፤ እነርሱም ምስረታ ወይም ጀማሪ /Start-up/ ደረጃ፣ ታዳጊ ወይም መስፋፋት /Growth/ ደረጃ፣ እና መብቃት /Maturity/ ደረጃ ናቸው፡፡ በመሆኑም ይህንን የኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጃ ክፍፍል መሠረት በማድረግ ኢንተርፕራይዞቹ በየዕድገት ደረጃቸው የሚያስፈልጓቸው ድጋፎች መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በዚሁ መሰረት የኢንተርፕራይዞች የዕድገት ደረጀ ሽግግር መስፈርቶች፣ በመስፈርቶቹ መሰረት በሚኖሩ የኢንተርፕራይዝ የዕድገት ደረጃዎች የሚሰጡ የድጋፍ ማዕቀፎች እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ትርጓሜ

  1. ጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ ማለት የኢንተርፕራይዙን ባለቤት፤ የቤተሰብ አባላትና ተቀጣሪ ሰራተኞች ጨምሮ እስከ አምስት ሰዎች ቀጥሮ የሚያሰማራና የጠቅላላ ካፒታሉ መጠን ህንፃን ሳይጨምር በአገልግሎት ዘርፍ ከብር 50000 (ሃምሳ ሺ) ወይም በኢንዱስትሪ ዘርፍ ከብር 100000 (አንድ መቶ ሺ) ያልበለጠ ኢንተርፕራይዝ ነው፡፡

  2. አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ማለት የኢንተርፕራይዙን ባለቤት፤ የቤተሰብ አባላትና ተቀጣሪ ሰራተኞችን ጨምሮ ከስድስት እስከ ሰላሳ ሰዎች የሚያሰማራና የጠቅላላ ካፒታሉ መጠን ህንፃን ሳይጨምር በአገልግሎት ዘርፍ ከብር 50001 (ሃምሳ ሺህ አንድ) እስከ 500000 (አምስት መቶ ሺህ) ወይም በኢንዱስትሪ ዘርፍ ከብር 100001 (አንድ መቶ ሺህ አንድ) እስከ 1500000 (አንድ ሚልዮን አምስት መቶ ሺ) ያልበለጠ ኢንተርፕራይዝ ነው፡፡
  3. ገበያ ማለት በአካባቢ በክልልና በሀገር አቀፍና በውጪ ሀገር ደረጃ የሚገኝና የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በምርትና አገልግሎት በዋጋ ተወዳዳሪ ሆነው የሚቀርቡበት መንገድ ነው፡፡
  4. የገበያ ትስስር ማለት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በአካባቢ፤በክልልና ሀገርአቀፍ እና እንዲሁም በውጪ ሀገር በሚፈጠሩ የገበያ እድሎች በነጻ ገበያ መርሕ ላይ በተመሰረተ የገበያ ውድድር የእርስበርስ (በተዋረድ) ትስስር የሚፈጥሩበት፤ከመካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች፤ ከመንግስትና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች በንዑስ ተቋራጭነት፤በአውትሶርሲንግ፤በፍራንቻይዚንግ በአውትግሮዊነንግና በሌሎችችም የግብይት ዘዴዎች ተሳስረው ምርትና አገልግለት በማቅረብና በመቀበል የሚደረግ ትስስር እንዲፈጥሩ ድጋፍ ማድረግ ማለት ነው፡፡
  5. የክልል ገበያ ትስስር ማለት ከአዲስ አበባ ክልል ውጪ በየትኛውም የሀገሪቱ ክልል ከሚገኝ ማንኛውም የመንግስት ድርጅት፤መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት፤የመካከለኛና ከፍተኛ ኢንድሰትሪ ወይም የህብረት ሥራ ዩኒዮን በአዲስ አበባ ከተማ ካሉ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ጋር በገበያ ማስተሳሰር ነው፡፡
  6. "የውጪ ገበያ" ማለት የሥራ ቦታውን ከሀገር ውጪ ያደረገ የውጪ ካምፓኒ በአዲስ አበባ ከተማ ካሉ የጥቃቅንንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ጋር በተለያዩ የግብይት ስርዓቶች የሚደረግ የገበያ ትስስር ማለት ነው፡፡
  7. "ንዑስ ስራ ተቋራጭነት" ማለት የመካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ወይም የመንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድጅቶችን በከፊል በመለየት ሥራውን በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ውል በመፈጸም የሚካሄድ የግብይት ሥርዓት ነው፡፡
  8. "አውትሶርሲንግ" ማለት በመንግስታዊ፤መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት እና ኩባንያዎች የሚከናወኑ ተግባራትን በመለየትና በማውጣት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ምርቱ ውይም አገልግሎቱ በጥቃቅንና አነስተኛ የሚቀርብበት የግብይት ስርዓት ነው፡፡
  9. "ፍራንቻይዚንግ" ማለት በተወሰኑ ለየት ባሉ ምርቶች ወይም አገልግሎቶች ከአምራቹ ወይም አገልግሎት ሰጪው ወይም አከፋፋዩ ድርጅት ጋር የንግድ ስምምነት ውል በመፈጸም በውሉ መሰረት በውል ሰጪው የንግድ ስም፤ምልክትና ፈቃድ የሚፈጸም የንግድ አሰራር ስርዓት ነው፡፡
  10. " አውትገሮወር" ማለት በአግሮፕሮሰሲነግና በማኔፋክቸሪንግ ሥራ ላይ የተሰማሩ መካከለኛና ከፍተኛ ኢንተርፕራይዞችን የሚያስፈልጓቸውን ግብዓቶች በቀጥታ ከማምረት ይልቅ ምርቱን በከፊል በማምረት ለሌሎች እሴት በመጨመር ያለቀለትን ምርት ለገበያ እንዲያቀርቡ በከፊል የተጠናቀቀ ምርት ማቅረብ የማድረግ ስራ ነው
  11. "ኢንተርፕረነርሽፕ" ማለት አንድ ኢንተርፕራይዝ በተሰማራበት ዘርፍ ገበያ ለማግኘት የሕብረተሰቡን የምርትና የአገልግሎት አቅርቦት ፍላጎት በመለየት እንዲሁም ተወዳዳሪዎችንና የገበያ ድርሻቸውን በመለየት ስለ አዋጭነቱ መተማመን ደረጃ ሲደረስ ምርትና አገልግሎት ሥራ የመሰማራት ክህሎት ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡
  12. "ቴሌማርኬቲንግ" ማለት በስልክ ደንበኞችን በመለየት የምርት ናሙና የሚያስተዋውቁበት እና ሽያጭ የሚካሄድበት የግብይት መንገድ ነው፤
  13. "ጥሬ ዕቃ" ማለት አንድን ምርት ለማምረት ወይም አገልግሎት ለመስጠት የምንጠቀምበት ግብዓት ነው፤
  14. “ፕሮሞሽን” (የምርት ወይም የአገልግሎት ማስተዋወቂያ ዘዴዎች) ማለት ምርትን ወይም አገልግሎትን ለማስተዋወቅ የመገናኛ ብዙሃን፣ ንግድ ትርዒትና ባዛር፣ ብሮሽር፣ ቢዝነስ ካርድ፣ ቋሚ የማስታወቂያ ሰሌዳ፣ ማሸጊያ እና የመሳሰሉትን የካትታል፡፡

የገበያ ልማትና የግብይት ሥርዓት መርሆዎች

ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራዞች የሚደረገው የገበያ ልማትና ግብይት ድጋፍ አፈጻጻም የሚከተሉት መርሆዎች ይኖሩታል፤
    1. የሚሰጡ የገበያ ድጋፎች የጠባቂነትን አመለካከት የሚያነጥፉና ኢንርተርፕራይዞቹ ችግራቸውን በመለየትና መፍትሔ በማፈላላግ ሂደት ውስጥ ግንባር ቀደም የሚሆኑበት
    2. የሚሰጡ የገበያ ድጋፎች በግልፅ መስፈርት ላይ የተመሠረቱ፣ የኢንተርፕራይዞችን የዕድገት ደረጃ ከግምት ያስገቡ፣ የተቀናጁና ተወዳዳሪነትን የሚያጎለብቱ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣
    3. የአካባቢ የገበያ ዕድሎችን አሟጦ መጠቀም፤
    4. በጥራትና በዋጋ ላይ የተመሰረተ የገበያ ተወዳዳሪነትን መከተል፣
    5. የንግድ አሰራርን መሠረት ያደረገና ተጠያቂነት ያለው የግብይት ሥርዓት መፍጠር፣
    6. ትኩረት ለተሰጣቸው የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው አቅም እንዲፈጥሩ ማስቻል፤
    7. የመንግስት ፕሮጀክቶችን የገበያ ትስስር ድጋፍ ፍታዊ በሆነ መልኩ እንደየእድገት ደረጃቸው ለኢንተርፕራይዞች ቅድሚያ መስጠት፤
    8. እያንዳንዱ ኢንተርፕራይዝ ለሚወስዱት የገበያ ትስስር ሃላፊነትና ተጠያቂነት መሰረት ያደረገ ይሆናል

    የጥቃቅንና አነስተኛ የመካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎችን በገበያ ስለማስተሳሰር

    በየደረጃው የሚገኙ የገበያ ልማት ባለሙያዎች በየጊዜው በአከባቢ ተጨባጭ የገበያ እድሎችን በመለየትና በማጥናት ኢንተርፕራይዞች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚከተሉት ተግባራት ይከናወናሉ፤
    1. በአካባቢው በየዘርፉ ተሰማርተው የሚገኙ አነስተኛ፤መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎችን በዝርዝር የመለየት ሥራ መስራት
    2. በየዘርፉ የተለዩ ኢንዱስትሪዎችን የምርት ወይም የአገልግሎት መጠን፤ ዓይነት፤የጥራት ደረጃ፤የማቅረቢያ ዋጋ፤ወዘተ የመለየት ሥራ መስራት
    3. ኢንዱስትሪዎቹ ከጥቃቅንና አነስተኛ የሚፈልጉትን ግብዓት ወይም ምርት ወይም አገልግሎት በዝርዝር መለየት
  1. በየዘርፉ የተደራጁና ከላይ ከ1-3 የተለዩትን ዝርዝር መረጃዎች መሠረት በማድረግ ሊተሳሰሩ የሚችሉ ኢንተርፕራይዞችን ፕሮፋይል ብቃት ያላቸውን ኢንተርፕራይዞች በስራው ባህሪና በሚፈለገው የኢንተርፕራይዞች የእድገት ደረጃ በመለየት ስለትስስሩ ግንዛቤ መፍጠር ይኖርበታል፡፡
  2. ከከተማው የንግድና ዘርፍ ማህበራት ጋር የቅርብ ግንኙነትና የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም በስሩ ካሉት የንግድ ድርጅቶች፤አማካሪዎችና ባለሙያዎች ጋር በመነጋገር በጥቃቅንና አነስተኛ እንዲሁም በመካከለኛና በከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች መካከል የሚፈጠረውን ትስስር ማሳደግ
  3. በየደረጃው ያሉ ኢንተርፕራይዞች በአካባቢው ካሉ ኢንዱስትሪዎች ጋር ላመስተሳሰር የሚያስፈልጋቸው የክህሎት፤የፋይናንስ፤የቴክኖሎጂ፤የቦታና ሌሎች ድጋፎች የሚፈልጉ ሆኖ ሲገኝ ድጋፉ የሚቀርብበትን ሁኔታ በዝርዝር በመለየት ለድጋፍ ሰጪ (የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ) ባለሙያዎች መረጃውን በማስተላለፍ በእድገት ደረጃቸው መሠረት ክፍተቱን እንዲሞላ መደረግ ይኖርበታል
  4. ክፍተታቸው ተሞልቶ ዝግጁ የሆኑ ኢንተርፕራይዞችን የገበያ ባለሙያ ገበያው የማስተሳሰሩን ሥራ ያከናውናል፡፡
  5. ከመካከለኛና ከፍተኛ ኩባንያዎች የቀረበ ሥራ ከአንድ በላይ የሆኑ ኢንተርፕራይዞች ሊሰሩት የሚገባው ከሆነ በሶስትዮሽ ውል መፈጸም የሚቻል ሲሆን በሶስትዮሽ ውል መፈጸም ካልተቻለ አንድ ኢንተርፕራይዝ ሥራውን በውል ተቀብሎ ሌሎች ተመሳሳይ ደረጃ ያሉ ኢንተርፕራይዞች በንዑስ ተቋራጭነት ወይም በሌሎች የትስስር መንገዶች ተዋውለው ሥራውን እንዲሰሩ ሁኔታውን እንዲመቻች መደረግ ይኖርበታል፡፡
  6. የገበያ ትስስሩን ለመፍጠር የሚያስችል እድል ተፈጥሮ ነገር ግን ግብዓት ለማምረት የሚያስፈልግ የጥሬ እቃ ፍላጎት ሲፈጠር ጥሬ እቃው ከሚገኝበትን ፋብሪካዎችና አምራች ድርጅቶች በማነጋገር የገበያ ልማት ባለሙያ እንዲያመቻች ድጋፍ ይደረጋል፡፡
  7. በአካባቢው ከውጪ የሚገቡ ነገር ግን በሀገር ውስጥ ሊመረቱ የሚችሉ ምርቶችን ለመለየት (በሱፐርማርኬቶች፤በሆቴሎች፤በሱቆች ወዘተ) በዝርዝር በማጥናት መረጃውን በየዘርፉ ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች እንዲደርሳቸው ይደረጋል፡፡
    (መጠነ ሰፊ ከሆኑት ጥቃንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አደራጅተን በጋራ እድሉን እንዲጠቀሙ ማድረግ)

ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በአካባቢ የሚፈጠር የገበያ ትስስር ዓይነቶች

  1. መንግስታዊ ከሆኑ ተቋማት ጋር የሚፈጠር የገበያ ትስስር፤
  2. መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር የሚፈጠር የገበያ ትስስር፤
  3. ከፍተኛና መካከለኛ ኢንድስትሪዎች ጋር የሚፈጠር የገበያ ትስስር፤
  4. በኢንተርፕራይዞች መከካል እርስ በርስ የሚፈጠር የገበያ ትስስር፤
  5. ከሸማቾች መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበራት እንዲሁም ከዩኒየኖች ጋር የሚፈጠር የገበያ ትስስር፤
  6. ከአካባቢ ማህበረሰብ ጋር የሚፈጠር የገበያ ትስስር፤
  7. ከግለሰቦች ጋር የሚፈጠር የገበያ ትስስር፤
  8. የፋይናስ ተቋማት፤ ከግል ንግድ ድርጅት ተቋማት ጋር የሚፈጠር የገበያ ትስስር፤
  9. ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ በተቋማት ወይም ወኪሎች መካከል የሚካሄድ ትስስር፤
  10. በቴሌ ማርኬቲንግ የሚፈጠር የገበያ ትስስር፤
  11. በኤሌክትሮኒክስ ግብይት የሚፈጠር የገበያ ትስስር፡፡

በመንግስት ተቋማት በሚፈጠሩ የገበያ ድጋፎች ኢንተርፕራይዞች ወይም ኢንደስትሪዎች ምልመላ እንደሚከተለው ይሆናል፡-

  1. የገበያ ዕድሉን የሚፈጥረው ተቋም በሚያወጣው መስፈርት መሰረት ማከናወን አለበት፤
  2. ገበያውን የፈጠረው ተቋም የሚያወጣቸው መስፈርቶች ከኢንተርፕራይዞች ወይም ኢንደስትሪዎች የዕድገት ደረጃ ጋር የማይገናዘቡ ሆኖ ሲገኝ ገበያውን ከሚፈጥረው ተቋም ጋር በመወያየት በሚዘጋጁ መስፈርቶች መሰረት የሚፈጸም መሆን አለበት፤
  3. የገበያ ዕድሉን የሚፈጥረው ተቋም መስፈርት ሳያዘጋጅ ስራውን ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች ወይም ኢንደስትሪዎች መስጠት የፈለገ ከሆነ ያደራጃቸው አካል ስራው ከሚጠይቀው የሰው ኃይልና ካፒታል አንፃር መስፈርት በማዘጋጀት የሚፈጸም መሆን አለበት፤
  4. ኢንተርፕራይዙን ወይም ኢንደስትሪዎችን ያደራጀው አካል የመመልመያ መስፈርቱን ግልጽ በማድረግ በውድድር ሊይ ተመስርቶ የሚፈጸም መሆን አለበት፤
  5. የመመልመያ መስፈርቱ ለኢንተርፕራይዞች ወይም ኢንደስትሪዎች ግልጽ ሆኖ የሚቆይበት ጊዜ የገበያ ዕድሉን የሚፈጥረው ተቋም በሚያዘጋጀው መስፈርትና የጊዜ ሰለዳ መሰረት የሚፈፀም መሆን አለበት፡፡

በወረዳ ደረጃ የሚሰሩ ተግባራት

  1. በአካባቢ ገበያ ልማት ላይ ያተኮረ የአካባቢ ገበያ ጥናት ማካሄድ
  2. በጥናቱ ውጤት መሠረት ኢንተርፕራይዞችን እርስበርስ(ጀማሪውን ከታዳጊው፤ከበቃው ወዘተ) የማስተሳስር ሥራ መስራት
  3. ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፐራይዞችን በአካባቢው ከሚገኙ መካከለኛ ወይም ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች በተለያየ አግባብ የሚተሳሰሩበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ሁለቱንም አካላት የሚፈልጉትን መለየት፤የማወያየትና ትስስር የሚፈጠርበትን ስልት መቀየስ
  4. በአካባቢው የሚገኙ የመንግስት፤የግልና ሌሎች ድርጅቶች ለጥቃቅንና አነስተኛ በንዑስ ተቋራጭነት፤በአውትሶርሲንግ፤በሌሎችም የትስስር ስርዓቶች ተሳስረው የሚሰሩበትን ሁኔታ ማመቻቸት
  5. በአካባቢው የሚገኙ ኢንተርፕራይዞችን ምርትና አገልግሎቶች ፕሮፋይል በማዘጋጀት ሥራ ሊሰጡ ወይም ምርትና አገልግሎት ሊወስዱ የሚችሉ ድርጅቶች በልዩ ልዩ ዘዴ የማስተዋወቅ
  6. በኢንዱስትሪ ማዕከላት በመገኘት ኢንተርፕራይዞች የሚያስፈልጋቸውን የጥሬ እቃ አይነት በመጠን በዋጋና በጥራት ደረጃ በዝርዝር በመለየት ጥሬ እቃው የሚገኝበትንና በጅምላ ግዢ እንዲፈጽሙ ምክርና አድጋፍ ማድረግ
  7. በወረዳ ደረጃ ወይም በአጎራባች ወረዳዎች ጋር በመተባበር ኤግዚብሽንና ባዛሮችን ያስተዋውቃል
  8. በገበያ ልማትና ግብይት ሂደት የተሻለ እንቅስቃሴ ያደረጉና ሞዴል የሚሆኑ ኢንተርፕራይዞችን በመለየት ተሞክሮ ያሰፋል
  9. በየወሩ የገበያ ልማት እንቅስቃሴን በተመለከተ ለክፍለ ከተማ ሪፖርት ያቀርባል
  10. የገበያ ትስስር የሚደረግለት ለእያንዳንዱ ኢንተርፕራይዝ ለምንያህል ጊዜ ገብያ ትስስር እንደተፈጠረላቸው ሙሉ መረጃውን በተደራጀ ና ገላጭ በሆነ መንገድ እንዲዲያዝ ማድረግ
  11. በወረዳ ደረጃ የሚዘጋጁ ባዛሮችና ተሳታፎዎችን በመለየት በተመደበለት መደበኛ በጀት በዕቅድ መሰርት ወቅቱን ጠብቆ እንዲፈፀም ያደርጋል
  12. ከቤቶች ልማት ፕሮጀክት እና ተመሳሳይነት ካላቸው ስራዎች ጋር ተያይዞ በሚደረገው ድጋፍ በህንፃ ስራ ተቋራጭና በጥቃ/አነስ/ኢንተር/ የሚሰሩ ስራዎችን በመለየት በሚመለከታቸው የስራ ድርሻ ብቻ ድጋፍ ማድረግ
  13. በኢንተርፕራይዞች በገበያ ሂደት በሚደረጉ ድጋፎች ለተገልጋዩች ተደራሽ ላማድረግ በሙሉ ሃላፊነትና ተጠያቂነት የሚያስፈልጉ አገልግሎቶችን በመለየት ድጋፍ ይደረጋል

የገበያ ድጋፍ ተጠቃሚዎች መብትና ግዴታ

የገበያ ድጋፍ ተጠቃሚዎች መብት
    • ወቅታዊ የገበያ መረጃ ማግኘት
    • የንግድ ስራ አመራር ስልጠና ድጋፍ ማግኘት
    • አገልግሎቱን በአካባቢ ገበያ ማስተዋወቅ የምችልበት በተዘጋጁ ኤግዚብሽንና ባዛር ላይ የማሳተፍ
    • በመንግስትም ሆነ በግል ተቋማት በአገር ውስጽም ሆነ በውጪ አገር በሚፈጠረው የገበያ ትስስር በተቀመጠው በእድገት ደረጃና የድሀጋፍ መጠን መሰረት ፍትሃዊ የሆነ ድጋፍ ማግኘት
    • በተለያዩ የመንግስት ፕሮግራሞች (ስልጠና፣ስብሰባ፣ልዩ ድጋፍ…ወዘተ) በሚመለከታቸው ላይ የመሳተፍ መብት

    የገበያ ድጋፍ ተጠቃሚዎች ግዴታ

    • መንግስት በሚያደርገው ድጋፍ ተጠቃሚ ለመሆን ለሚያስፈልጉ ወቅታዊና ህጋዊ መረጃዎች የማቅረብ
    • በተፈጠረው ገበያ ደረጃውን የጠበቀ ተወዳዳሪ አገልግሎት መስጠት
    • በመንግስትም ሆነ በግል ተቋማት የተፈጠረ የስራ ዕድል በውሉ መሰረት አገልግሎት መስጠት
    • ከኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብ በጸዳ በልማታዊ አስተሳሰብ አገልግሎት የመስጠት
    • ማንኛውም ጥቃቅንና አነስተኛ ያገኘውን የገበያ ዕድል ለአደራጅ አካል የማሳወቅ ግዴታ (መረጃ የመስጠት)
    • በጨረታ ሂደት ካለፉ ለአደራጁ መ/ቤት የቅድመ ክፍያ ዋስትና የማቅረብ ግዴታ
    • በጨረታ ያለፉትን ተግባር በጥራት ሰርቶ የማስረከብ
    • በጨረታው ሂደት ሲሳተፉ በተመጣጣኝ ዋጋ የማቅረብ
    • የአገልግሎት ሰጪ ተቋምን የሠራተኛ ሙያዊ ክብርን የመጠበቅ
    • በሚዘጋጁ ኤግዚብሽንና ባዛር ላይ የተሰጠን ቦታ ለሌላ ወገን ያለማስተላለፍ
    • በኤግዚብሽንና ባዛር ላይ ለማቅረብ ስም ዝርዝራቸውን ካስያዙ በኋላ በቂ ምርት ይዞ መገኘት
    • በተመዘገቡበት ኤግዚብሽንና ባዛር ላይ ከዘርፉ ውጪ ሌላ ምርት ያለማቅረብ
    • ጨረታ ያለፈበትን ቦታ የሰብ ኮንተርራት ውል የገባበትን የማቅረብ

ለበለጠ መረጃ ገበያ ልማትና ፕሮሞሽን መመሪያ ይጫኑ።

ተያያዥ መረጃዎች
© 2023 Yeka woreda 7 Labor E/I/D/Office. Designed by 0912689710