አገራችን ኢትዮጵያ የበለጸገችና መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ በማሰለፍ የህዝቧን የኑሮ ሁኔታ ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማሻሻል የሚያስችል መዋቅራዊ አደረጃጀት በመፍጠር ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ሀገራዊ የድህነት ቅነሳ ግብን ለማሳካት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡ በወረዳችንም የአስተዳደሩን ትኩረት የሚሹ እና በተደራጀ የልማት እና መልካም አስተዳዳር ዕቅድ ምላሽን የሚጠይቁ በርካታ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮች በመኖራቸውና የጥቃቅን ፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ለኢኮኖሚያዊ ፣ለማህበራዊና ፖለቲካዊ ዕድገት በተለይ ለኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ ትግበራ መሳካት ያለውን ፋይዳ ግምት ውስጥ በማስገባት ከመቸውም ጊዜ በላይ በበቂ አካላዊ እና ስነልቦናዊ ዝግጅት ወደ ትግበራ ገብተናል፡፡

ተያያዥ መረጃዎች
© 2023 Yeka woreda 7 Labor E/I/D/Office. Designed by 0912689710