መግቢያ

የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ተጠቃሚዎችን በአራት የተለያዩ ክፍሎች በመለየት ድጋፍ የሚሰጥ ሲሆን እነሱም የአካባቢ ልማት፣ የቀጥታ ድጋፍ፣ ልዩ ድጋፍ የሚሹ እና የኑሮ ማሻሻያ ናቸው፡፡ የአካባቢ ልማትና የኑሮ ማሻሻያ የስራ ክፍሎች ተደጋጋፊ ሆነው ተግባራዊ የሚደረጉ ሲሆን የመስራት አቅም ያላቸውንና በተለያዩ ምክንያቶች በዝቅተኛ የኑሮ ደራጃ ላይ የሚገኙ ተጠቃሚዎችን በተለያዩ የአካባቢ ልማት ስራዎች ተሰማርተው ከሚያገኙት ገቢ ጥሪት አፍርተው በቀጣይ ራሳቸውን ችለው ኑሮዋቸውን ለማሻሻል የሚያስችላቸውን ሁኔታዎች በማመቻቸት ከፕሮግራሙ እንዲመረቁ የሚያግዙ የስራ ክፍሎች ናቸው፡፡ በተለይም የኑሮ ማሻሻያ የስራ ክፍል ዋነኛ ዓላማ የተጠቃሚዎችን እና የቤተሰቦቻቻውን የገቢና የኑሮ ሁኔታ በዘላቂነት ማሻሻልና ራሳቸውን ማስቻል ነው፡፡ በዚህም መሰረት በክፍሉ የሚሰጠው አጠቃላይ ድጋፋ ዓላማዎችን ለማሳካት የሚረዱ ናቸው፡፡

የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ዋና ዋና ዓላማዎች

ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራዞች የሚደረገው የገበያ ልማትና ግብይት ድጋፍ አፈጻጻም የሚከተሉት መርሆዎች ይኖሩታል፤
    1. የተጠቃሚዎችን የስራና የቁጠባ ባህል በማዳበር ራሳቸውን እንዲችሉ የጥሪት ማፍሪያ ስራዎች ላይ እንዲሰማሩ ማድረግ፤
    2. ተጠቃሚዎችን በመሰረታዊ የህይወት ክህሎቶች በማነጽ በግል ስራ እና በቅጥር ሊሰማሩበት የሚፈልጉትን አዋጭ የስራ መስክ በመለየት ቀጣይ ህይወታቸውን የሚመሩበትን ሁኔታ ማመቻቸት የሚገጥማቸውን ችግር በራሳቸው አቅም በመፍታት በዘላቂነት ራሳቸውን እንዲችሉ ማድረግ፤
    3. ተጠቃሚዎችን በተገቢው ጊዜ ከፕሮግራሙ እንዲመረቁ ማድረግና ለምረቃው የሚያስፈልጉ መረጃዎች ማደራጃት፤

    የኑሮ ማሻሻያ መሰረታዊ መርሆዎች፡

    1. ፍላጎት ተኮር /Demand driven/፡- ተጠቃሚዎች በራሳቸው ወይም በቅጥር ስራ ለመሰማራት ምርጫው በቤተሰቡ ፋላጎት የሚከናወን ሲሆን የቤተሰቡ አባላት ይጠቅመናል ብለው የሚያስቡትን የስራ መስክ ያለማንም ተጽዕኖ አማራጮችን በመመርመር በራሳቸው ፍላጎት የሚመርጡ ይሆናል፡፡
    2. ለተጠቃሚዎች የሚሰጥ ድጋፍ በግለሰብ ደረጃ መሆኑ /Individual and tailored support/፡- በዚህ ፕሮግራም ተሳታፊዎች በቡድን የሚሰራ ስራ እንዲመርጡ የተቀመጠ አሰራር የለም፡፡ በቤተሰብ ደረጃ ከሚመርጡት የስራ መስክ ውስጥ የራሳቸውን ስራ የሚመርጡ /ለምሳሌ፡ አነስተኛ ንግድ/ ወይም በቅጥር ስራ የሚሰማሩ/ ለምሳሌ፡ በአሽከርካሪነት በድርጅቶች መቀጠር/ ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህም መሰረት ተጠቃሚዎች በመረጡት ማንኛውም የስራ መስክ ቢሰማሩ ተገቢውን ድጋፍ የሚያገኙ ይሆናል፡፡ ለአሰራር አመቺ ይሆን ዘንድ ተመሳሳይ የስራ ምርጫ ያላቸውን ተጠቃሚዎች ለስራቸው ድጋፍ የሚሆን ስልጠና በጋራ የሚሰጣቸው ይሆናል፡፡
    3. ቀላልና ምቹ አሰራር መዘርጋት /Simple and client-friendly/ - የንግድ ስራ እቅድና የስራ ትስስር ዕቅድ በተጠቃሚዎች የሚዘጋጅ ሲሆን በአንድ ማእከላትና በሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ይደረጋል፡፡
    4. ተለዋዋጭነት /Flexibility/፡ የተጠቃሚዎች የኑሮ ማሻሻያ የስራ መስክ ምርጫዎች በቅጥርና በግል የስራ መስክ በሚል በሁለት የተከፈለ እና አንዱ ከአንዱ የተለየ ቢሆንም ተያያዥነት ግን አላቸው፡፡ ለምሳሌ አንድ ለግል የስራ ዘርፍ በእንጨት ስራ የሰለጠነ ተጠቃሚ በዚያ መቀጠል ካልፈለገ በሌላ ድርጅት በቅጥር ስራ ሊሰማራ የሚችል ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በቅጥር ስራ ለመሰማራት በአሽከርካሪነት የሰለጠነ ተጠቃሚ ለድርጅት ከመቀጠር ይልቅ በግል የታክሲ ስራ ላይ ለመሰማራት ይችላል፡፡
    5. ለአካባቢ ጥበቃና ለሴቶች ትኩረት የሚሰጥ መሆን /Climate smart and gender sensitive/ ለግል ስራ የሚመረጡ የስራ መስኮች ዝቅተኛ የአካባቢ አየር ንብረት ተጽዕኖ ያላቸው መሆን የሚጠበቅባቸው ሲሆን የሴቶችን ተሳትፎ የሚያበረታቱና የአካባቢውን እሴቶችን የጠበቁ ይሆናሉ፡፡
    6. በተጨባጭ መረጃ ላይ የተመሰረተ መሆን /Evidence based/: ፡ በዘላቂ ኑሮ ማሻሻያ ስራዎች ወደ ተግባራዊ እንቅሰስቃሴ ከመገባቱ በፊት አስፈላጊ የሆኑ መሰረታዊ መረጃዎችን በማሰባሰብና በመተንተን /ጥንካሬዎችን፣ ድክመቶችን መልካም አጋጣሚዎችና ስጋቶችን/ የመተንተን ስራ መሰራት አለበት፡፡
    7. መላመድ የሚችል /Adaptive/፡- የሚሰሩ ስራዎች ወቅታዊ የገበያ ሁኔታን ቴክኖሎጂንና የኢኮኖሚ እድገትን መሰረት ያደረገ መሆን አለበት፡፡
    8. ሃብትን ማቀናጀትና በማስተባበር መጠቀም /Integration and synergy of resources/ ፡- የአካባቢ ልማት ስራዎችን እና ሌሎች ተጓዳኝ ስራዎችን እንዲሰሩ ማስተባበርና በማቀናጀት እንዲሁም ሌሎች በኑሮ ማሻሻያ የሚሳተፉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም የሚሳተፉበትን መንገድ ይመቻቸል፡፡
    9. ቅደም ተከተሉን የጠበቀ የኑሮ ማሻሻያ ትግበራ /Careful sequencing and tracking of livelihoods interventions/፡- ቅደም ተከተሉን መሰረት ያደረገ ድጋፍ፣ ክትትልና ግምገማ በማድረግ በመረጃ ላይ የተመሰረተ የተጠቃሚዎች ምረቃ መካሄድ አለበት፡፡
    10. ለትምህርትና ለእውቀት ከፍተኛ ትኩረት መስጠት /Strong focus on learning and knowledge management

የዘላቂ ኑሮ ማሻሻያ የድጋፍ ዑደት(የትግበራ ምዕራፍ)

    የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ/የምግብ ዋስትና አስፈጻሚ አካላት የታችኛው መዋቅር እና ሌሎች ፈፃሚዎች ተጠቃሚ ቤተሰቦችን በቀጣይ ኑሯቸውን በዘላቂነት ሊያሻሽል የሚችል፣ በፕሮግራሙ ቆይታቸው አቅማቸውን ያገናዘበ እና በገበያ ተፈላጊና አዋጪ የሆነ የስራ መስክ እንዲመርጡ ተከታታይነት ያለው ድጋፍና ክትትል ማድረግ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ቤተሰቡ የንግድ ሥራ ዕቅድ / የሥራ ፍለጋ ዕቅድ እንዲያጋጅና ዕቅዶቹ እንዲፀድቁ እና የገንዘብ ድጋፍ እንዲለቀቅ መደገፍና መከታተል አለበት፡፡

ለበለጠ መረጃ የኑሮ ማሻሻያ የትግበራ ማንዋል ይጫኑ።

ተያያዥ መረጃዎች
© 2023 Yeka woreda 7 Labor E/I/D/Office. Designed by 0912689710