መግቢያ

ክፍለ ከተማችንና አገራችን ኢትዮጵያ የበለጸገችና መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ በማሰለፍ የህዝቧን የኑሮ ሁኔታ ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማሻሻል የሚያስችል መዋቅራዊ አደረጃጀት በመፍጠር ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ሀገራዊ የድህነት ቅነሳ ግብን ለማሳካት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ከሚገኙ ክፍለ ከተሞች ላይ ትገኛለች፡፡

መንግስት ሀገራችን ከነበረችበት ድህነትና ኋላቀርነት ለማላቀቅ የህብረተሰቡን የኢኮኖሚና ማህበራዊ የላቀ ተሳትፎና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ዘርፎችን እየለየና በሂደት ዘርፉን ውጤታማ ማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን በመቅረጽና ወደ ተግባር በመግባት ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋትና የበርካታ ዜጎችን የስራ አጥነት ችግር በመቅረፍ ኑሯቸው እንዲሻሻል እየተደረገ ይገኛል፡፡

የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት የዘርፉን አዲስ የልማት ስትራቴጂ ማጽደቅ ተከትሎ በአዲስ መልክ ተደራጅቶ በስትራቴጂው የተቀመጡ ተልዕኮዎችን ለመወጣት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ጽ/ቤቱ በተዋቀረው በእያንዳንዱ የስራ ሂደት መደባዉን ሳይጠብቅ አሁን ባለዉ አደረጃጀት ሊተገበሩ የሚገባቸውን ተግባራት ከከተማው መሪ እቅድና ከዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በመነሳት ዝርዝር እቅዶችን በማውጣት እየተገበረ ይገኛል፡፡

ጽ/ቤቱ ለተገልጋዮች የሚሰጠውን አገልግሎት ለማሻሻልና ለማቀላጠፍ የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ የቆየ ቢሆንም ተገልጋዮች ወደ ጽ/ቤቱ አገልግሎት ለማግኘት ሲመጡ የሚሰጣቸውን የአገልግሎት ዓይነትና ጥራት፤ የሚወስደውን ጊዜ አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስፈልጋቸው ወጪና እንዲሁም በእነርሱ በኩል ማሟላት የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታዎችን ያመላከተ የተገልጋዮች ቻርተር ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው፡፡

የጽ/ቤቱ ዓላማዎች

  1. ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር የህዝባችንን ገቢ ማሻሻል ድህነትን መቀነስ፣ እንዲሆም ፍትሓዊ የሀብት ክፍፍል እንዲፈጠር ማድረግ
  2. ዘርፉ ተወዳዳሪና ቀጣይነት ያለው ልማት የሚያስመዝግብ የገጠር ልማትን ለማስቀጠልና ለኢንዱስትሪው ልማት አሰተማማኝ መሰረት የሚጥል ዘርፍ እንዲሆን ማስቻል፣
  3. በከተሞች ሰፊ መሰረት ያለው ልማታዊ ባለሀብት በመፍጠር የዘርፉን ልማት ማስፋፋት ናቸው፡

ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች

  1. የሥራ ስምሪት በማስፋፋት የስራ ዕድል መፍጠር
  2. መሰረት የሚጥል ዘርፍ እንዲሆን ማስቻል፣
  3. በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚ ማድረግ
  4. የመስሪያ ቦታ ልማትና አቅርቦት
  5. ምቹ የሥራ ቦታና አካባቢ መፍጠር
  6. የዜጎች ስምምነት ሰነድ ዓላማ

    1. ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ያለው የአሰራር ስርአት ለማስፈን፣
    2. አገልግሎት አሰጣጡ በተጠናው ስታንዳድ መሰረት እንዲሰጥ ለማድረግና፣
    3. በስታንዳርዱ መሰረት አገልግሎት የማይሰጡ አካላት ላይ ተጠያቂነትን በማስፈን የመልካም አስተዳደር ቸግሮችን መፍታት ናቸው፡፡
    4. በጽ/ቤቱ በሚሰጠው አገልግሎት ላይ ተገልጋዮችን ለማሳተፍ፣
    5. ሁሉም ተገልጋዮች በስራ ኢንተርፕራይዝ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የባለቤትነት ስሜት ተሰምቷቸው አስተያየት ጥቆማና ማናቸውንም ግብዓት በነጻነት የሚሰጡበትን ሁኔታ ለማመቻቸትና ለመተግበር ነው፡፡

    የተቋሙ ራዕይ፣ ተልዕኮና እሴቶች


    አዲስ አበባ ከተማ በ2022 ምቹ የስራ ሁኔታ የተረጋገጠባት ፤ ዘላቂና አስተማማኝ የስራ እድል የፈጠሩ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪዎች ያደጉባት ከተማ ሆና ማየት ነው ፡፡

    የስራ ስምሪት አገልግሎትን በማስፋፋት፤ ሰላማዊ የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነትን በማስፈን ለስራ ፈላጊው ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር፣የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም በመተግበር ከድህነት ወለል በታች የሚገኙ ነዋሪዎችን ኑሮ ማሻሻል እንዲሁም የመስሪያ ቦታ፣ የፋይናንስ፣ የካፒታል ሊዝ፣ የገበያ፣ ቴክኖሎጂ፣ የቴክኒክና ምክር ድጋፍ በማድረግ ኢንተርፕራይዝና አምራች ኢንዱስትሪ በምርትና ምርታማነት ብቁና ተወደዳሪ እንዲሆኑ ማስቻል፡፡

    ስራ ፈጣሪነትን ማበረታታት፣

    ግልጽና አሳታፊ ተጠያቂነትን ማስፈን፣

    ቅንጅታዊ አሰራርን ማጎልበት፣

    ሁልጊዜም ከተግባር መማር፣

    የላቀ አገልግሎት መስጠት፣

    ፍትሃዊ የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፣

    ፈጣን የቴክኖሎጂ ሽግግርን ማረጋገጥ፣


    የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት

    የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት በዝርዝር ለማወቅ ከፈለጉ ይህን Duties and Responsibility ይጫኑ

    የተገልጋዮች መብትና ግዴታዎች

    መብቶች

    1. በጽ/ቤቱ ውስጥ የሚገኙ የዘርፉን ልማት የተመለከቱ መረጃዎችን የማግኘት፤
    2. ምንም ልዩነት ሳይደረግበት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የመሆን፣
    3. ማንኛውም ተገልጋይ በአገልግሎቱ አሰጣጥና በአገልግሎት ሰጪው ቡድን/ሠራተኛ ላይ ያለውን አስተያየትና ቅሬታ የማቅረብ፣
    4. በጽ/ቤቱ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ዝርዝር የማወቅና የመጠቀም፤
    5. ተገቢ የሆነ ድጋፍና እገዛ የማግኘት፤
    6. ቀልጣፋ አገልግሎት የማግኘት፤
    7. ለሚያቀርቡት ቅሬታዎች የመደመጥና ምላሽ የማግኘት ፣
    8. በውይይት መድረኮች መሳተፍና አስተያየት ማቅረብ

    ግዴታዎች

    1. ሕጎችንና የአሰራር መመሪያዎችን መከተል
    2. ለሚፈልጉት አገልግሎት የተሟላና ትክክለኛ መረጃ የማቅረብ፣
    3. ተገልጋዬች አገልግሎት ለማግኘት ሲመጡ
      ተፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን የማሟላት

    ተግባራትና ስታንዳርድ

ተያያዥ መረጃዎች
© 2023 Yeka woreda 7 Labor E/I/D/Office. Designed by Markos Mulat G